የውሃ ጉድጓድ መቆፈር
ከተራራ ላይ በፓራሹት መዝለል ከውሃ ጉድጓድ መቆፈር ጋር ምን ያገናኘዋል? ሳም ሃርዲ እና ናታን ጆንስ በአፍሪካ ካሉት እጅግ ከፍተኛ ገደሎች መዝለል ይችሉ እንደሆነ ጽፈው ሲጠይቁን፣ «ይቻላል፤ ግን መጀመሪያ ከፓርኩ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገር አለባችሁ» አልናቸው። የፓርኩ ጠባቂዎችም በጥበብ ወጣቶቹ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ምን ማበርከት እንደሚችሉ ጠየቁ፤ መልሱም በአቅራቢያው ላለችው ሚሊገብሳ መንደር የውሃ ጉድጓድና ፓምፕ ሆነ።



